ቢኒያም ታደለ

@binu_tadele

film maker writer ✍️ director 🎬 producer 🤓
Followers
1,086
Following
933
Account Insight
Score
25.84%
Index
Health Rate
%
Users Ratio
1:1
Weeks posts
77 4
22 days ago
የመስቀሉ ዝምታ ​በዕለተ ዓርብ ፀሐይ ፊቷን በጨለማ ከናነበች ፍጥረት ሁሉ በፈጣሪው ሕማም ተናወጠ። ንጉሥ ሆኖ ሳለ የሾህ አክሊልን የታገሰ ዳኛ ሆኖ ሳለ በዓመፀኞች እጅ የተፈረደበት ያ ድንቅ ምስጢር በመስቀል ላይ ተገለጠ። ​በግዕዝ እንዲህ ይነገራል፡ ​"ወበሳድስት ሰዓት ኮነ ጽልመት ዲበ ኩላ ምድር እስከ ተሰዓት ሰዓት፤ ወጸርሐ ኢየሱስ በዓቢይ ቃል ወይቤ፡ ኤሎሄ ኤሎሄ ለማ ሰበቅታኒ?" (ትርጉም በስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ። በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?" ብሎ ጮኸ።) ​በዚያ ሰዓት በመስቀሉ ዙሪያ የነበረው ድባብ የሥቃይ ብቻ አልነበረም የፍቅር እንጂ። ደሙ ወደ ምድር ሲንጠባጠብ ,የአዳም ዕዳ ተሰረዘ። ጌታችን በገዛ ፈቃዱ ነፍሱን አሳልፎ ሲሰጥ, ሞት በሞቱ ተሸነፈ። ​ እጆቹ ዓለምን ለመደገፍ የተዘረጉ ነበሩ እነዚያው እጆች ግን በመስቀል ላይ ተቸነከሩ። እግሮቹ ለሰው ልጅ ሰላምን ለማብሰር ይፈጥኑ ነበር እነዚያው እግሮች ግን በችንካር ቆሰሉ። ጎኑ በጦር ተወጋ፤ ከዚያም የሕይወት ምንጭ ፈሰሰ። ​ይህ ዕለት የጥላቻ ድል ሳይሆን, የማይለካው መለኮታዊ ፍቅር በታሪክ መድረክ ላይ የታየበት ታላቅ ትዕይንት ነው። በዝምታው ውስጥ ጩኸት፣ በሞቱ ውስጥ ትንሣኤ፣ በውርደቱ ውስጥ ክብር አለ። ​"ስብሐት ለከ ኦ ዘተሰቀልከ በእንቲአነ!" (ስለ እኛ ለተሰቀልከው ላንተ ምስጋና ይሁን!) ✍️ቢኑ ዘንኩ እንኳን አደረሳችሁ
16 0
1 month ago
ደህና ይግጠምሽ epilogue @mesay__tefera ከዓመታት በኋላ የጊዜ ሽንፈትና የትዝታው ትንሳኤ ከአሥር ዓመታት በኋላ፣ ያ የቆሰለ ልብና የደረቀ እንባ ትዝታ ብቻ ሆኖ አልቀረም። ዓለም በራሷ ፍጥነት እየተሽከረከረች፣ አማንን እና እሷን በተለያዩ የሕይወት ጎዳናዎች ላይ አውርዳቸዋለች። አንድ ቀን አመሻሽ ላይ፣ በከተማዋ ጥግ በሚገኝ ትንሽ የቡና ቤት ውስጥ፣ አማን ብቻውን ተቀምጦ ሲጋራ እያጨሰ በመስኮት በኩል የሚወርደውን ዝናብ ያስተውላል። አሁን ጎልማሳ ሆኗል፤ በፊቱ ላይ ያሉት የጭንቀት መስመሮች የሕይወትን ውጣ ውረድ ይተርካሉ። ድንገት የቡና ቤቱ በር ሲከፈትና አንዲት ሴት ስትገባ የልቡ ምት ባልተለመደ ሁኔታ ጨመረ። እሷ ነበረች። አልሸሸችም፤ አልደነገጠችም። ይልቁንም ረጅም ዓመታት በውስጧ ያቆየችውን ከባድ ሸክም አውርዳ እንደጣለች ሰው፣ ቀስ ብላ ወደ እሱ ጠረጴዛ አመራች። "ሰላም ነው አማን?" አለች ድምፅዋ በብስለት ተኩሎ። አማን ፈገግ አለ። ያ የድሮው የቁጭት ፈገግታ ሳይሆን፣ ሁሉንም ነገር የተረዳና ይቅር ያለ ሰው እርካታ ነበር። "ደህና ነኝ... አንቺስ ደህና ነሽ?" በመካከላቸው የነበረው ያ የተሰበረ ፅዋ ዛሬ የለም። ይልቁንም አዲስና ጠንካራ የሆነ የሰውነት ክር ተተክቷል። እሷ በሄደችበት ዓለም ብዙ አይታለች፣ እሱም በቆመበት ደጅ ብዙ ተምሯል። የሰው አፍ ሊያቆስላቸው የሞከረው ያኔ ነበር፤ ዛሬ ግን ማንም ስለ እነሱ ወሬ የለውም። ጊዜ ሁሉንም ነገር በዝምታው አክሞታል። "ያኔ 'የሸኘ ደጁን አያምንም' ብለህ ነበር..." አለችው አይኖቿን ወደ መስኮቱ እያዞረች። አማን መለሰላት "አዎ፣ ያኔ ደጁን የማላምነው ትመለሻለሽ ብዬ ሳይሆን፣ ትዝታሽ በዚያ ደጅ አልፎ ልቤን ይሰርቀዋል ብዬ በመስጋት ነበር። ዛሬ ግን ደጁም፣ ልቡም፣ ትዝታውም ሰላም አግኝተዋል።" በዚያች ምሽት የተረዱት ትልቅ እውነት ቢኖር እውነተኛ ፍቅር አይሞትም፣ ቅርጹን ይለውጣል እንጂ። ከፍቅረኝነት ወደ ባዕድነት፣ ከባዕድነት ወደ መከባበር፣ ከመከባበር ደግሞ ወደ ረቂቅ መንፈሳዊ ትስስር ተሸጋግረዋል። እሱ የተመኘው 'ደህና ይግጠምሽ' የሚለው ጸሎት ደርሶ፣ እሷም በሰላም ተመልሳለች። ቡናቸውን ጠጥተው ሲለያዩ፣ እንደ ድሮው የስንብት ህመም አልነበረም። ይልቁንም ለዓመታት የተዘጋ መጽሐፍ ተከፍቶ፣ የመጨረሻው ምዕራፍ ተጽፎ እንደተዘጋ ታላቅ እፎይታ ነበር። "ሌላ ሌላው ነገር ይቅር... የቀረው ትዝታ ይበቃል" አማን ወደ ቤቱ ሲያመራ፣ ዝናቡ ቆሞ ነበር። የጨረቃዋ ብርሃን መንገዱን ሲያበራው፣ እሱም ለራሱ እንዲህ አለ፦ "ጊዜ ያልፈቀደው ፍቅር፣ በጊዜ ሂደት ወደ ትልቅ ጥበብ ተቀይሯል።" #music #story
19 0
2 months ago
ይሄ ደግሞ የሄደችው ሴት perspective ይመስለኛል የሄደችው ነፍስ ትረካ (ደህና ይግጠምሽ) ክፍል 2 @mesay__tefera መንገዱ ረጅም ነው። ወደ ኋላዬ ብመለከት የማየው አማን የቆመበትን ደጅ ሳይሆን፣ በጭጋግ የተዋጠ የትዝታ ተራራን ነው። እግሮቼ ወደ ፊት እየተራመዱ ቢሆንም፣ ልቤ ግን እዚያው የቀረ ይመስለኛል። ሰዎች "ሄደች" ይላሉ፤ እኔ ግን "ተሰደድኩ" ነው የምለው ከራሴ ፍቅር ወደ ራሴ ባዶነት። "እንዴት እንደመጣ ስህተቱ..." ብሎ ሲጠይቅ በዝምታ መመለሴ ስለማልወደው አልነበረም። ይልቁንም፣ እውነቱ ከቃላት በላይ ስለከበደኝ እንጂ። አንዳንድ ጊዜ ፍቅር በራሱ ስህተት ይሆናል—ጊዜው ያልፈቀደው፣ ቦታው ያልመደበው። እኔና አማን የነበረን ግንኙነት እንደ ክረምት አበባ ነበር፤ ውብ ቢሆንም ብርዱ ግን ሊገድለው ግድ ነበር። ቃሌን ቀይሬ ብመለስ እንኳን፣ የተሰበረው የፍቅር ፅዋ መልሶ ውሃ አይዝም። የተሰነጠቀ መስተዋት መልክን ያዛባል፤ እኔ ደግሞ በአማን አይን ውስጥ ተሰባብሮ መታየትን አልፈለግሁም። በከተማው ውስጥ ስሜ ሲነሳ፣ ስሜቴ እንደሚቆስል አውቃለሁ። የሰው አፍ እንደ ምላጭ ስለታም ነው። "ተይው ምን ያደርጋል" ሲለኝ የሰማሁት ድምፅ ግን የቁጣ ሳይሆን የርኅራኄ ነበር። አማን ለኔ ያለው ፍቅር የሚገለጸው እኔን በማሰር ሳይሆን፣ በክፉ እንዳይነኩኝ በጸሎት በማጠር ነው። "ደህና ይግጠምሽ" ሲለኝ፣ በቃላቱ ውስጥ የነበረው 'እወድሻለሁ' የሚል ትርጉም ልቤን እንደ መርፌ ወጋው። የሸኘ ሰው ደጁን አያምንም፤ እኔ ግን የሸኘኝን ልብ አምናለሁ ከኔ በላይ ለኔ የሚሳሳ መሆኑን። እሱ ህመሙን ደብቆ በዝምታ ሊኖር ሲወስን፣ እኔ ደግሞ ብቸኝነቴን ስንቅ አድርጌ ልጓዝ ወሰንኩ። የሰጠሁት ብርታት እሱን ለመርሳት ይርዳው ሲል፣ እኔ ግን የሰጠኝን ፍቅር እንደ መቅረዝ ይዤው እሄዳለሁ። ቀናት ቀናትን ሲተኩ፣ ልቤ ከእሱ እንደራቀ ቢሰማውም፣ ርቀቱ ግን የቦታ እንጂ የነፍስ አይደለም። በፍቅራችን ፅዋ ውስጥ የቀረው የመጨረሻው ጠብታ 'ይቅርታ' ነው። እሱ እኔን ይቅር ሲለኝ፣ እኔም ራሴን ይቅር እንድል መንገድ ከፈተልኝ። "ላንቺ አይስጥሽ የኔን እጣ" የሚለው ቃሉ በጆሮዬ ያቃጭላል። እሱ ለኔ ሲል መከራን ለመቀበል ሲዘጋጅ፣ እኔ ግን ላለመጎዳት ራሴን አሳልፌ ሰጠሁ። በሄድኩበት ክፉ እንዳይነካኝ ሲመኝ፣ እኔም በእሱ ውስጥ የቀረው የኔ ትዝታ እንዳያቆስለው እመኛለሁ። ሌላ ሌላው ነገር ይቅር... ታሪካችን በዝምታ ይረቅ። እሱ በቆመበት ደጅ፣ እኔ በሄድኩበት ጎዳና—ሁለታችንም የጊዜ እስረኞች ነን። ስኳን አወጣች እና ኤርፎኗን ሰከሰታ ደህና ይግጠምሽ የሚውን የመሳይ ተፈራን ዘፈን ከፍታ እያዳመጠች ሌላ ሌላው ነገር ይቅር አይነገር ምንም ቢኖር ጥፋት አልይ ያንቺን ጉዳት ልቡሽ ወዶ ሰው አይጣ ላንቺ አይስጥሽ የኔን እጣ እዚህ ጋር ሲደርስ እንባዋ ሳታስበው ወረደ....... #music #story
9 0
2 months ago
የትዝታው ጥላና ያልተቀዳው ፅዋ #ክፍል1 ፀሐይ በደብረ ጥቁር ተራሮች ጀርባ ልትደበቅ ስትታገል፣ በሰማዩ ጠርዝ ላይ የሚታየው ቀይ ቀለም የቆሰለ ልብ ደም ይመስል ነበር። አማን በመስኮቱ አጠገብ ቆሞ የሚወርደውን ጭጋግ በትዝታ አይኖቹ ይከታተላል። የክፍሉ ዝምታ የሚሰበረው አልፎ አልፎ በሚሰማው የንፋስ ሽውሽውታ ብቻ ነው። በጠረጴዛው ላይ የተቀመጠው የጠሰበረ የቢራ ጠርመስ እና የጭሰው ያለቁ ሲጋራዎች ብቻ ናቸው። ስብርባሪው የአማንን ተበትነው የሚወጉት ለፍቅር ፅዋ ይመስላሉ ። "ልሰማ አልጓጓሁም..." አለ አማን ከመሳይ ተፈራ ዘፈን የተዋሰውን ግጥም ለራሱ በለገመ ድምፅ። ምክንያት ፍለጋ መባዘን የቆሰለን እጅ በጨው እንደማሸት መሆኑን ተረድቷል። ፍቅር ሲመጣ እንደ ንጋት ጤዛ ያለ ጥሪ ቢመጣም፣ ሲሄድ ግን በምክንያት ሰንሰለት ታስሮ እንዲቆይ መሞከር የሞኝነት ጫፍ ነው። እውነቱ ቃል ላይ ሳይሆን ከቃል በስተጀርባ ባለው ባዶነት ውስጥ ሰፍሯል። ጊዜ ያልፈቀደው ፍቅር፣ እንደማይበቅል ዘር መሬት ውስጥ ተቀብሮ መቅረት እንዳለበት አምኗል። ውጭ ያለው ዓለም ግን እንደ አማን ዝምተኛ አይደለም። የከተማው ወሬኞች ስለ እሷ "እንዲህ ሆነች... እንዲህ አደረገች" እያሉ መርዛቸውን ይረጫሉ። አማን ግን የራሱን ህመም ወደ ጋሻነት ቀየረው። "የሰው አፍ እንደ ሰደድ እሳት ነው፤ ቆንጆውንም ሆነ አስቀያሚውን አመድ ያደርጋል፣" ሲል አሰበ። ምንም እንኳን በመካከላቸው ያለው ድልድይ ቢፈርስም፣ እሷ ግን በዚያ ድልድይ ማዶ በሰላም እንድትኖር ይመኛል። "ክፉሽን አልየው" የሚለው ቃል ከአንደበቱ የሚወጣው እንደ ጸሎት ነበር። የሸኘ ሰው ደጁን አያምንም፤ ምክንያቱም ደጁ የናፍቆት መግቢያ፣ የስጋትም መውጫ ነውና። አማን የሄደውን ሰው የመውቀስን ባህል አጥብቆ ይፀየፋል። "ሄደች" ማለት "ሞተች" ማለት አይደለም፤ ወይም "ጠላችኝ" ማለት ብቻ አይደለም። "የራሷን መንገድ መረጠች" ማለት ነው። እውነቱን አውቆ፣ ህመሙን እንደ ውድ ሀብት ደብቆ፣ ዝምታን ስንቅ አድርጎ ለመኖር ወሰነ። ለዓመታት የሰጠችው ብርታት ዛሬ እሷን ለመርሳት መገልገያ መሆኑ ትልቅ ተቃርኖ ቢሆንም፣ የሰው ልጅ ልብ ግን እንዲህ ናት በሰጠችው እጅ ትነጥቃለች። "የሞት ያህል ሀዘኑ ቢከፋ... አይሆንም ከይቅርታ በላይ" አማን በመጨረሻ የተረዳው ትልቅ ፍልስፍና ይህንን ነው። ጥላቻ እስረኛ ያደርጋል፤ ይቅርታ ግን ነፃ ያወጣል። እሷ የራሷን እጣ ፈንታ ስትከተል፣ እሱም የእሱን እጣ ይቀበላል። "ላንቺ አይስጥሽ የኔን እጣ" ሲል የመጨረሻውን የደህና ሁኚ ቃል ተነፈሰ። ይህ ቃል የመሸነፍ ሳይሆን፣ የፍቅር የመጨረሻውና ረቂቁ ደረጃ ነበር። እሷን ከራሱ እስር ነፃ አወጣት፤ እራሱንም ከትዝታው ሰንሰለት ፈታ። አማን ትንሽ አበሱ አደረገና ድንገት አንድ ሀሳብ እንደመጣለት ሰው ወደ እስፒከሩ ተራምዶ ስልኩን Bluetooth connect አድጎ የመሳይ ተፈራን ሙዚቃ ከፈተና መሬቱ ላይ ዝርፍጥ ብሎ ቁጭ አለና ከደረት ኪሱ Winston ሲጋራ አውጥቶ ለኮሰ.. @mesay__tefera
91 0
2 months ago
እድልነው (አዲስ ለገሰ) @addis_leggese ባለአራት ማዕዘኗ አሮጌ ቴፕ፣ በክፍሉ ጥግ ካለው አቧራማ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጣለች። ካሴቱ ሲሽከረከር የሚፈጥረው የለሰለሰ ድምፅ፣ በክፍሉ ውስጥ ካለው የብቸኝነት ፀጥታ ጋር ይደባለቃል። መስኮቱ ጋ ቆሞ ወደ ውጭ የሚመለከተው አብርሃም፣ የድምፃዊው የቁጭት ዜማ በልቡ ውስጥ እንደ ትኩስ ፍም ሲነድ ይሰማዋል። ​ይህ ግጥም ለእሱ ተራ የሙዚቃ ግጥም አይደለም፤ የነፍሱ ስንጥቅ የታተመበት ሰነድ እንጂ። ​"ዕድል ነው እጣ እጣ... የማይወጣ" የሚለው ስንኝ ሲሰማ፣ አብርሃም እጆቹን ወደ ኋላ አቆራኝቶ ትንፋሹን ዋጥ አደረገ። ሕይወት ልክ እንደ ቁማር ጠረጴዛ ሆናለች - እጁ ላይ የወደቀው ካርድ የማይቀየር፣ የገጠመው እጣ ደግሞ የማይሻር። እጣው ላይ የወጣው 'ቁጣ' ነበር፤ እርሷን የማጣት ቁጣ። ​በክፍሉ ውስጥ የሚንሳፈፈው "እህህ..." የሚለው ዜማ፣ ልክ እንደ መቃብር ቤት ማሚቶ በውስጡ ያስተጋባል። "የሆነው አይታፈስም" ሲል ግጥሙ፣ አብርሃም የፈሰሰ ውሃን ለማጥለቅ እንደሚሞክር ሰው የባከኑ ቀናቱን በምናቡ ሊሰበስብ ይሞክራል። የእርሷ ውሳኔ ልክ እንደ ሰም የታሸገ ደብዳቤ ነው  የማይታጠፍ፣ የማይቀደድ። ​አብርሃም ወደ ቴፑ ጠጋ ብሎ ድምፁን ከፍ አደረገው። "መች አገኘን አንዲት አፍታ፣ ለልብ ወሬ ለይቅርታ" የሚለው ስንኝ ሲመጣ፣ ልቡ በሀዘን ክር ተተበተበ። ይቅርታ የሚባለው ድልድይ ሳይገነባ፣ በመካከላቸው ያለው የልዩነት ገደል ሰፋ። እርሷ ለአዲስ ምዕራፍ 'አላሚ' ስትሆን፣ እርሱ ግን በቆየው ምዕራፍ መጨረሻ ላይ እንደ ነጥብ ተገትሮ ቀርቷል። እርሷ የወደፊቱን ዜማ ስታዜም፣ እርሱ ካለፈው ትዝታ ጋር ይጫወታል። ​በጣም የሚያመው ግን ዝምታዋ ነው። ግጥሙ እንደሚለው "ዝምታሽ ይበልጥ አመመኝ"። ዝምታዋ እንደ ተሳለ ቢላዋ በየቀኑ ትንፋሹን ይሰርቀዋል። መጮህ፣ መጣላት፣ መከራከር ይቻል ነበር፤ ነገር ግን እርሷ ዝምታን እንደ ጋሻ ለብሳለች። ያ ዝምታ ደግሞ ከሺህ ቃላት በላይ የሚከብድ ቅጣት ሆኖበታል። ​ቴፑ መሽከርከሩን ቀጥሏል። "ጉዳት ነው አዳማጭ የሌለው"። አዎ፣ አብርሃም አሁን የቆሰለ ተዋጊ ነው፤ ግን ቁስሉን የሚያይለት፣ ህመሙን የሚሰማለት ሰው የለም። በትንሿ ክፍሉ ውስጥ፣ ከአሮጌው ቴፕና ከሚንቀጠቀጠው የካሴት ድምፅ ጋር ብቻውን የቁጭት ግብግብ ይገጥማል። ​ካሴቱ አልቆ "ጠቅ" የሚል ድምፅ ሲያሰማ፣ ክፍሉ በድጋሚ በፀጥታ ተዋጠ። አብርሃም ግን አሁንም እዚያው ቆሟል። በጆሮው ውስጥ አሁንም ያ ዜማ ያቃጭላል... "እድል ነው እጣ እጣ... የማይወጣ"። ህይወቱ በዚያች አጭር ግጥም ውስጥ ታስራ የቀረች መሰለው፤ የማይፈታ እንቆቅልሽ፣ የማይመለስ ትላንት። ሙዚቃውን ከእንደገና ፈተው እና መፅሐፍ መደርደሪያው አጠገብ ካለች ወዝ የጠገበች አሮጌ ባለእንጨት ሶፉ ላይ ዝርፍጥ ብሎ ቁጭ አለና አይኑን ጨፍኖ በዜማው ፍሰት ነጎደ....... 1/07/18 ✍️ ቢኑ ዘንኩ
21 1
2 months ago
የቃልኪዳን መቃብር (እስኪ አትማኝ) #@fikeraddis.nekatibeb ቤቱ በዝምታ ተውጧል። በመስኮቱ በኩል የሚገባው የድንግዝግዝ ብርሃን በክፍሉ ውስጥ ካለው ብቸኝነት ጋር ተዳብሏል። እሷ ግን ቁጭ ብላለች በእጆቿ መካከል የሚንቀጠቀጥ ብዕር በልቧ ውስጥ ደግሞ የሚናጥ የቃላት ማዕበል አለ። ለዓመታት "የፍቅር ሀገር" ብላ በገነባችው ዓለም ውስጥ ዛሬ ባዕድ ሆናለች። ያኔ፣ ፍቅር ገና ሲጀመር፣ ዓለሟ በእሱ ስም የተገደበ ነበር። እሱ ለእሷ "መነሻም መድረሻም" ነበረ። ነገር ግን ያ የገነባችው ማማ ዛሬ በእሬት መራርነት ተለውጧል። ፍቅር አንስቶ መሬት ሲጥላት፣ የወደቀችበት ምድር እንደ ማር ይጥም የነበረው ትናንት አልፎ ዛሬ እንደ እሬት የሚመረግዝ መራር እውነት ሆኖባታል። "እስኪ አትማኝ..." ስትል በወረቀቱ ላይ አስፈረች። ይህ ቃል ለምላሱ የቀረበ ተራ ተማጽኖ አልነበረም ይልቁንም ክብሯን ለማስጠበቅ የምታደርገው የመጨረሻው የነፍስ ትግል እንጂ። "ስሜን ተጠንቅቀህ ያዝልኝ" ስትል የጋራ ትዝታቸውንና በስሟ ውስጥ የታተመውን የእሱን ጥላ ከላዩ ላይ እንድታራግፍ እየጠየቀችው ነበር። ልቧ እንዲህ ሲል አጉረመረመ 'እንዴት ያለ የማይዝል ልብ ቢኖርህ ነው? ፍቅርን እንደ ሩቅ መንገድ የምትጋዘው መጨረሻ የሌለው የጥፋት ጉዞ የምትጓዘው አንተ ማን ነህ?' እውነቷን ሲቀማት በውሸት ካባ ስሟን ሲያቆሽሸው ታያለች። የቆሰለችው ግን በመከዳቷ ብቻ አይደለም ገና ሳታገግም በእንባ እየታጠበች እንኳ እርሱን "ለማማት" አለመፈለጓ የውስጥ ማንነቷን ልዕልና ያሳያል። እሷ የእሱን ክፋት በክፋት ለመመለስ የምትቸኩል አይደለችም ይልቁንም የእሱን ማንነት አውቃ "የማትጨበጥ የማትነካ" ደመና መሆኑን ተረድታ መገላገልን መርጣለች። በመጨረሻም ብዕሯን አሳረፈች። የመጨረሻው መስመር ላይ "በቃኝ እኔስ ቻው ቻው" ስትል ቃላቱ እንደ ሰንሰለት መበጠስ ድምፅ በክፍሉ ውስጥ አስተጋቡ። ይህ የሽኝት ቃል ሳይሆን ከማያባራ የልብ ስብራት የምትወጣበት የነፃነት አዋጅ ነበር። የፈራችው አልቀረምጨእሱ መሄዱን አላቆመም። እሷ ግን ዛሬ እሱን ማቆም ትታ፣ ራሷን ለማዳን ፊቷን አዞረች። በረንዳው ላይ ወጥታ ወደ አድማሱ ስትመለከት ከእንግዲህ የእሱ "ክፉ ነገር" የማይደርስበት አዲስ ንጋት እንደሚጠብቃት ተሰማት። ይሄ ዘፈን ላይ ያለችው ሴት የዘፈኑን ግጥም በዚህ አይነት መንፈስ ውስጥ ሆና እሯሷ የፃፈቸው ይምስኛል እኔ 30/06/18 ቢኑ ዘንኩ ✍️ #ቢኑ_ታደለ #ፍቅራአዲስነቃጥበብ
30 5
2 months ago
ትዝታ እንደ በረሃ ንፋስ ​በቤቱ ውስጥ ያለው ብቸኝነት እንደ ከባድ ጭጋግ ክፍሉን ወርሶታል። ሰዓቱ እኩለ ሌሊት አልፏል፤ ብርሃኑ ደብዝዞ የሚታየው የድሮ ቴፕ መቅጃ ግን ያቺን "ናፍቆቶ ነው ያስቸገረኝ..." የምትለውን ዜማ በዝግታ ያንቆረቁራታል። በረከት ሶፋው ላይ ተዘርሯል፤ አይኖቹ ግድግዳው ላይ ቢተከሉም፣ ልቡ ግን ርቆ ሄዷል። ​ ​የዘፈኑ ግጥም "ተረስቶ የቆየው ትዝታዋ ዛሬ" ሲል፣ በረከት የልቡ መዝገብ ድንገት ተገለጠበት። ለዓመታት በአቧራ ተሸፍኖ የነበረው ትዝታዋ፣ እንደ በርበሬ አይኑን ማቃጠል ጀምሯል። ፍቅር እንደ ወይን ነው ይባላል—ሲቆይ ይጣፍጣል፤ ትዝታ ግን እንደ እሳት ነው—የቆየ ቁስልን ያቃጥላል። ​ያቺን ወጣት የረሳት መስሎት ነበር። በጊዜ ማዕበል ተገፍተው፣ በኑሮ ሩጫ ተራርቀው፣ ስሟን እንኳ ከአንደበቱ ካጠፋው ቆይቷል። ነገር ግን ዛሬ፣ በዚች ጭር ባለች ሌሊት፣ ድምጿ እንደ ንጋት ጤዛ በምናቡ ፈሰሰ። "ፍቅርዬ" የምትልበት ያች ቃና፣ በጆሮው ውስጥ እንደ ሸክላ ሙዚቃ እያቃጨለች አስቸገረችው። ​ ​ናፍቆት እንደ እንግዳ ነው። ሳይጠሩት ይመጣል፣ የልብን ደጃፍ በርግዶ ይገባል፣ ከዚያም እንደ በረሃ ንፋስ የነፍስን ሰላም ጠርጎ ይወስዳል። በረከት አሁን እያደረገው ያለው ይሄንኑ ነው። ሳቅናፈገግታው በአእምሮው ሰሌዳ ላይ እንደ ሲኒማ ፊልም ይገለጣሉ። ያን ጊዜ አብረው ሲሆኑ ዓለም የቆመች ትመስል ነበር። ዛሬ ግን ያ ርጋታ የለም፤ ያለው የጥያቄ መዓት ብቻ ነው። "ምን ሆና ይሆን?" "የት ትኖር ይሆን?" ​ ​ሙዚቃው ሲደጋገም በረከት አይኑን ጨፈነ። ግጥሙ እንደሚለው፣ ሌሊት በህልሙ እየመጣች የምታውከው ትዝታ አሁን በቁሙም መጥታለች። እጆቹን ወደ ባዶው አየር ዘረጋ፤ ነገር ግን የሚጨብጠው ነገር የለም። ትዝታ ማለት እኮ መያዝ የማይቻል ጭስ፣ ግን ደግሞ ትንፋሽ የሚከለክል ከባድ ስሜት ነው። ​በመጨረሻም፣ ሙዚቃው ጋብ ሲል ቤቱ ይበልጥ ጸጥ አለ። በረከት ለራሱ በሹክሹክታ እንዲህ አለ፦ "ፍቅር መረሳት አይችልም፤ ለጊዜው ይተኛል እንጂ፣ አንድ ቀን እንደ ቀብር አፈር ተገፍቶ ይወጣል።" --- ​ 27/06/18 ቢኑ ዘንኩ✍️
17 0
2 months ago
የአለት ላይ አሻራ ​ ​ታሪክ ራሱን ይደግማል ይባላል፤ ነገር ግን በካራ ማራ ተራራዎች ላይ የተፃፈው ታሪክ ፈጽሞ የማይደበዝዝ የኢትዮጵያዊነት ማኅተም ነው። ​የሶማሊያ ወራሪ ጦር በኢትዮጵያ ላይ በከፈተው መጠነ ሰፊ ጥቃት ወቅት የፖለቲካ ልዩነት ሳይገድባቸው ኢትዮጵያዊያን በአንድነት የቆሙበት ትልቅ አጋጣሚ ነበር። ​ ካራ ማራ ለጠላት የማይደፈር ምሽግ ለኢትዮጵያ ጀግኖች ደግሞ የድል አውድማ ሆኖ አልፏል። ያ የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የጥቁር ህዝብ ኩራት ዳግም የታየበት ቀን ነው። ​የመተካት ተምሳሌት፦ የካራ ማራ ድል የጥንቶቹን የአድዋ ጀግኖች መንፈስ ወጣቱ ትውልድ ተረክቦ ለዓለም ያሳየበት ክስተት ነው። ​ክብር ለሀገር ፍቅር ሲሉ ለወደቁት ጀግኖቻችን! 🕯️🇪🇹 ​#Ethiopia #Karamara #Unity #History #EastAfrica #ኢትዮጵያዊነት
74 4
2 months ago
የእናንዬ ልጅ የቀመጢና 50 ሰው ገሎ አለ በጤና ኧረ ሰውየው! የቀትር ጮራ የሚያርበደብድ ስሙ ሲጠራ አናት ወራሪ እንደ ቀን ፀሀይ ሲጥል ነው እንጅ ሲሄድ አይታይ የሚሰባብር እንደ በረዶ የአጋሰስ መንጋን የሚያደርግ ነዶ
67 5
2 months ago
የጋራው ጥላ ​ፀሐይዋ እየጠለቀች የው ደንገዝገዝ ብሏል የአቶ በቀለ ጥላ ከጀርባቸው በበሩ የመንደር መብራት አማካኝነት ከፊታቸው ረዝሞ ይታያል። ያ ጥላ ግን የእሳቸው ብቻ አይመስልም። ለዓመታት "ደህና ነኝ" በሚል ጭንብል ውስጥ ደብቀውት የኖሩት ብቸኝነት፣ ቤታቸው ሲገቡ ከሚጠብቃቸው ዝምታ ጋር ተደባልቆ እንደ ጉም ይከብዳቸዋል። ​"መሽቶብኛል መሰል ፈራሁ መመላለስ" አሉ ለራሳቸው በለሆሳስ። እድሜያቸው መግፋቱን ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ውስጣዊ ማንነታቸው ተመላልሰው የሚመለከቱበት ድፍረት ማጣታቸውን እያሰቡ ነበር። የገዛ ህመማቸውን እንደ እንግዳ ነገር ሽምጥጥ አድርገው በመካድ ኖረዋል። ​በድንገት ከመንገዳቸው ዳር ካለው ግቢ የለቅሶ ድምፅ ሰሙ። የማያውቁት ሰው ሞት ቢሆንም፣ እግራቸው ሳያስበው ወደዚያ አመራ። ​ተቀላቅለው ተቀመጡ። አንዲት እናት በከፍተኛ ድምፅ እየጮኹ ያለቅሳሉ። ያ ለቅሶ ግን ለእሳቸው እንግዳ አልነበረም። የሴቲቱ ድምፅ ውስጥ የሚንቀጠቀጠው ስብራት፣ አቶ በቀለ ለዓመታት የደበቁትን "የራስ ሃዘን" በረንዳ ላይ አውጥቶ ዘረገፉት። ​ሌላው ሰው ሲያለቅስ ሲያዩ፣ የገዛ ቁስላቸው መላወስ ጀመረ። ለካስ ሰው የራሱን እሳት የሚረዳው የሌላው ሲነድ ሲያይ ነው! • ​እውነታው፡ ለቅሶው የሟቹ ቢሆንም፣ እንባው ግን የሳቸው ነበር። የሰው ልጅ ስቃይ ሁሉ በአንድ ገመድ የተሳሰረ መሆኑን ተረዱ። ​አቶ በቀለ ከለቅሶ ቤቱ ሲወጡ ጨለማው የቀድሞውን ያህል አያስፈራም ነበር። "የሰው ለቅሶ ስደርስ" አሉ ቀና ብለው፣ "የራሴ ሃዘን ትርጉም ሰጠኝ።" ​ፍርሃት የሚመጣው ለብቻችን የቆምን ሲመስለን ነው። ህመማችን የሰው ሁሉ ህመም መሆኑን ስንረዳ ግን፣ ያ ግዙፍ ሃዘን ወደ ትህትና እና ወደ ሰላም ይለወጣል። ​ ይህንን ፅሁፍ ስፅፍ መነሻው የ Kirubal Zarfu ን መሽቶብኛል መሰል ፈራሁ መመላለስ የኔው ሀዘን ገባኝ የሰው ለቅሶ ስደርስ የሚለውን ግጥም ረጅም ኪሰላሰልኩት በኃላ ነው !!! I need ur opinion
10 0
2 months ago
🍋
344 5
3 months ago